Monday, October 12, 2020

የግእዝ ትምህርት ምዝገባ

 ሰላም ለክሙ 



ለ2021/2013 ዓ/ም የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ተመዝጋቢዎች ሁሉ 


1ኛ  የቅድመ ዝግጀት ትምህርት ስላለን ቶሎ በመመዝገብ ዝግጅት አድርጉ


2ኛ. በዌስተርን ዩኒየን እና በመኒግራም የምትከፍሉ ሁሉ መጀመሪያ እኔን በዋትስአብ ደውላችሁ ፣ በድምጽ፣ ወይም በጽሁፍ መልእት አነጋግሩኝ። በባንክ፣ በ"Zelle" እና በሌሎች ተመሳሳ መንገዶች የምትከፍሉ ግን የአካውንት ቊጥሬ ካላችሁ መካክና ደረሰኙን ወደ እኔ መላክ ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ


3ኛ. ሌላ የተሻለ መንገድ እየፈለግሁ ስለሆነ ለመጻሕፍት የተተመነውን ተጨማሪ ክፍያ እንዳትከፍሉ (ትምህርቱን ለመማር መጽሐፉን መግዛት አሁን ግዴታ አይደለም)


ሠናይ ለክሙ

ወእግዚአብሔር ምስሌክሙ

እም አውደ ጥናት ዘግእዝ


Friday, March 27, 2020

Corona Virus/ኮሮና ቫይረስ


Corona Virus/ኮሮና ቫይረስ ስያሜ የመተላለፊያ መንገዶች፣ መከላከያ እና ማብራርያ



Corona Virus/ኮሮና ቫይረስ ስያሜ የመተላለፊያ መንገዶች፣ መከላከያ እና ማብራርያ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ነው። ምሕረትና ቸርነት የባሕርዩ የሆነ ልዑል አምላክ በቸርነቱ ብቻ በሕይወት ጠብቆ ለዚች ቅጽበት ስላደረሰን የተመሰገነ ይሁን፤ አሁንም በማይለካው ፍቅሩ የተለመደውን ቸርነቱን አይንፈገን። ስለ እናቱ ስለ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምና ስለ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሁሉ ብሎ እንደ በደላችን አይቁጠርብን።

ዛሬ  ይህንን ቪዲዮ ያዘጋጀሁት ዓለምን ከዳር እስከዳር ስለ ተቆጣጠረው፤ ሰብአዊ ፍጡርን ሁሉ ስላስጨነቀውና ግራ ስላጋባው ተላላፊ ወይም ወረርሽኝ በሽታ የጤና ባለሙያዎች የሚናገሩትን በመተርጎም በተቻለኝ መጠን ግልጽና ቀላል በሆነ አማርኛ ለናንተ መረጃ ለመስጠት ነው። ይህ መረጃ የጤና ባለሙያዎች እና የአካባቢያችሁ ባለሥልጣናት ከሚሰጧችሁ መረጃ ጋር ተጨማሪ ሆኖ ሊረዳችሁ፤ ከዚህ በፊት የሰማችሁትን መረጃም  ሊያስታውሳችሁ የሚችል ነው ብየ አምናለሁ።
መጽሐፉን ለመግዛት ይህንን (ራሱ መጽሐፉን) ይጫኑት
የተላከብን ሕመም አዲስና መድሃኒት የሌለው መሆኑን ሁላችንም ሰምተናል። ስለዚህ መድኃኒታችን መድኃኒት ያልተገኘለትን ዓለም ያዳነው መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ መሆኑን እናምናለን፤ እውነትም ነው።

እግዚአብሔር ራሳችንን የምንጠብቅባቸው መሣሪያዎችን ማለትም እያንዳንዳቸውን የሰውነት ክፍሎቻችንን ሰጥቶናል። ስለዚህ በተቻለ መጠን እርሱ እንድንጠቀምባቸው የሰጠንን መሣሪያዎች እየተጠቀምን ራሳችንን ለመጠበቅ መዘጋጀትና ከአቅም በላይ የሆነብንን ደግሞ ሁሉን ለሚችል ለእርሱ መስጠት ይገባናል። ይህ የትክክለኛ አማኝ ሥራ ነው ብየ አምናለሁ።

እኔ የምሠራበት መሥሪያ ቤት ምድቡ ከጤና ማዕከላት ውስጥ ነው። ከ(CDC) ማለትም ከተላላፊ በሽታወች መቆጣጠሪያ ማዕከላት በጣም የቀረበ ክትትል የሚደረግበት መሥሪያ ቤት ነው። ስለዚህ የተሟላ መረጃ በየቀኑ ይሰጠናል። በመሆኑም እናንተም በተለያዩ መንገዶች መረጃውን የምታገኙ መሆናችሁን ባውቅም እኔም በበኩሌ የሰማችሁትን በተለያየ አቀራረብና መንገድ ደጋግማችሁ ብትሰሙት ይጠቅማል ብየ በማሰብ ነው። ያቀረብኩላችሁ እንደሚጠቅማችሁም ርግጠኛ ነው። ምክንያቱም መረጃን የመሰለ ነገር የለም ሲደጋገምም የበለጠ በአእምሮ ይቀረጻል እንጂ አይከፋም። እግዚአብሔር ሁላችንንም በቸርነቱ ይጠብቀን።
መጽሐፉን ለመግዛት ይህንን (ራሱ መጽሐፉን) ይጫኑት


በመጀመሪያ ከስያሜው እነሳለሁ
ስሙን “ኮሮና ቫይረስ” ስርጭቱን ደግሞ “ፓን ደሚክ” በማለት ይጠሩታል። የወረርሽኝን ሕመም “ኤፒ ደሚክ” እና “ፓን ደሚክ” በማለት ይጠሩታል። ቃላቱ መሠረታቸው ከግሪክ እና ከላቲን ነው። እኔ ግን የማውቀውን የክሪኩን ትርጉም እናገራለሁ።
ኤፒ-ደሚክ፡ = ባጭሩ ይዘታዊውን ትርጉም ስንናገር “አገር አቀፍ ወረርሺኝ” ልንለው እንችላለን
በአንድ አካባቢ፤ በአንድ አገር በሚኖር ሕብረተ-ሰብ ውስጥ የተከሰተና በፍጥነት የሚዛመት ተላላፊ ወይም ወረርሽኝ “ኤፒ ደሚክ” ይባላል።

የቃላቱን ትንታኔ በተመለከተ “ኤፒ” ማለት በ፤ በላይ፤ በውስጥ ወዘተ ማለት ሲሆን “ደሚክ” ማለት ደግሞ “ዲሞስ” ወይም “ዲሞቲክ” ከሚለው የግሪክ ቃል “ሕዝብ” ወይም “የሕዝብ” ማለት ነው። ስለዚህ “ኤፒ ደሚክ” ማለት በአንድ አካባቢ በሚኖር ብዙ ሕዝብ ላይ በፍጥነት የሚሰራች ወይም የሚዛመት ተሐዋሲ ወይም ወረርሽኝ ማለት ነው። “ተሐዋሲ” የምንለው ቫይረሱን ሲሆን “ወረርሽኝ” ስንል ደግሞ ስርጭቱን ነው።

ፓን ደሚክ፡ ደግሞ = ባጭሩ ይዘታዊውን ትርጉም ስንናገር “ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ” ልንለው እንችላለን
የቃላቱ ትንታኔ “ፓን” ማለት በግሪከኛ “ሁሉ”፡ማለት ነው። ለምሳሌ “ፓንዶክራቶስ” “ፓንዶ ዲናሞስ” ማለት ሁሉን የሚገዛ፤ ሁሉን ቻይ ወዘተ ማለት ነው። ስለዚህ “ፓን ደሚክ” ማለት ወይም ይሚባለው በአንድ አገር እና በአንድ አሕጉር ከሚኖር ሕዝብ አልፎ በአብዛኛው የዓለም ክፍል በሚኖር ሕዝብ ላይ በፍጥነት የሚዛመት ተላላፊ ብሽታ ነው።

አንድ ተላላፊ ሕመም ከአንድ አገር አልፎ ወደ ሌላው አገር ሲዛመት ማለትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲዳረስ ቢያንስ በአብዛኛው ዓለም ሲደርስ ስሙ ከ “ኤፒደሚክ” ወደ  “ፓን ደሚክ” ይቀየራል። ወይም ፓን ደሚክ ተብሎ ይጠራል። በቀላል አማርኛ “ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ” ማለት ነው። ይህንን ስያሜ የሚሰጠው የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ወይም ማዕከል ነው።

ታስታውሱ እንደሆነ ኮሮና ባይረስ ገና በቻይና ሲነሣ በሌሎችም የተወሰኑ አገራት ሲዛመት ስሙ ገና አልተቀየረም ነበር። “ኤፒ ደሚክ” የሚለውን ስም እንደያዘ ነበር። በኋላ ግን በአብዛኛው የዓለም ክፍል ሲሰራጭ “ፓን-ደሚክ” የሚለውን ስያሜ አገኘ።
እስከ አሁን ከዚህ በላይ የተነጋገርነው አንድ ተላላፊ በሽታ አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ስያሜ እንዴት እንደሚሰጠውና የስያሜው ትርጉም ምን እንደሆነ ነው።

ኮሮና ቫይረስ ምንድን ነው?

ኮሮና ባይረስ ባጭሩ ቅርጹን መሠረት አድርጎ የተሰየመ ሲሆን እንደ አክልል ክብ ስለሆነ ከቅርጹ በመነሳት “ክብ ወይም ዘውድ መሰል ቅርጽ ያለው ተሐዋሲ” ብለውታል ማለት ነው።

እንዴት ይተላለፋል?
በንክኪ እና በተለያየ መንገድ ቫይረሱ ወደ አካላችን ውስጥ ሲገባ ማለትም ከአካላችን ክፍት በሆኑ የአካል ክፍሎች አልፎ ወደ ውስጥ ሲገባ ማለት ነው፤ ለምሳሌ ክፍት የሆኑ የአካላችን ክፍሎች ከሚባሉት ዋና ዋና ዎቹ እና በቀላሉ ሊጋለጡ የሚችሉት “አፍ” አፍንጫ፤ እና “ዓይን” ናቸው። ሌሎችም እንዳሉን አትርሱ።

እንዴንት መከላከል ይቻላል?
ይህንን ቫይረስ ከምንከላከልባቸው መንገዶች ዋና ዋናዎቹ
1.  እጅን ለ20 ሰከንድ በሳሙና በደንብ መታጥብና ከታጠብን በኋላም በንጹህ ሶፍት ወይም ናብኪን ማድረቅ፤ ወይም ውሃ ካላገኘን በአልኮሆል ወይም የእጅ ማጽጃ (ሃንድ ሳኒታይዘር”) በደንብ መጥረግ።

ለምን እንታጠባለን? የእጅ መታጠብ ውጤት
ብዙ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ስለ ምንነካ ሰዎችን ስለምንጨብጭ ባይረሱ በእጃችን ላይ ይኖራል ወይም ይገኛል ተብሎ ይታመናል፤ ስለዚህ እጃችንን ለ20 ሰከንዶች በሳሙና እና በውሃ በምንታጠብ ጊዜ ወይም በአልኮል በምናጸዳው ጊዜ በእጃችን ላይ የነበረው ባይረስ ወይም ተሐዋሲ ይሞታል፤ ከሞተ ደግሞ ምንም የሚፈጥረው ሕመም አይኖርም።

2.  ከሰዎች ጋር አለመነካካት፡ ከሚስሉ እና ከሚያስነጥሱ ሰዎች በ6 ፊት ወይም ስድስት ጫማ ርቀት መሆን፤ ማለትም አለመቅረብ። ሰላምታችን ያለመነካካትና ያለ መቀራረብ በቃል ብቻ መሆን አለበት።

ለምን በርቀት መሆን አስፈለገ? ከሚስሉ እና ከሚያስነጥሱ ሰዎች በርቀት መሆን ያስፈለገበት ምክንያት ወይም የሚሰጠው ጥቅም፦ በምንስልና በምናነጥስ ጊዜ አፋችን እና አፍንጫችን ይከፈታል፤

በዚህ ጊዜ ፈሳሾች ከአፋችን እና ከአፍንጫችን ወጥተው በቅርበት ወዳሉ ሰዎች አካል ሊፈናጠሩና ወደ ሌላው ሰው አፍንጫና አፍ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ የሳለው ወይም ያስነጠሰው ሰው ኮሮና ቫይረስ ያለበት ከሆነ ቫይረሱ በምራቆቹ ወይም በፈሳሾቹ ውስጥ አብሮ አለ። ይህ ከሆነ ደግሞ ቫይረሱ ወደ አካላችን ከምራቆቹ ጋር ገባ ማለት ነው እንታመማለን።

3.  አፍን፤ አፍንጫን እና ዓይንን ባልታጠበ እጅ ከመነካካት መቆጠብ፡
ለምን? ባልታጠበ እጅ ፊትን በተለይ ክፍት የሆኑ አካላቶቻችንን ለምሳሌ አፋችንን፤ አፍንጫችንን፤ እና ዓይናችንን ባልታጠበ እጅ ከመነካካት መቆጠብ በቀላሉ በባይረሱ ከመጠቃት እንድናለን ። ከላይ እንዳየነው እጆቻችን ብዙ ነገሮችን ይነካካሉ ስለዚህ ቫይረሱ ያለበትን ነገር ለምሳሌ መዝጊያ፤ ጠረጴዛ፤ ወንበር ልብስ፤ የመኪና በር፤ ወዘተ ልንነካ እንችላለን፤ በዚህ ጊዜ ቫይረሱ ከነካነው ነገር ወይም አካል ወደ እጆቻችን ይሸጋገራል ማለት ነው።

 ከዚያ በኋላ ሳንታጠብ አፋችንን፤ አፍንጫችንን፤ እና ዓይናችንን ከነካን ቫይረሱን ወደ አካላችን ውስጥ አስገባነው ማለት ነው። ስለዚህ ባልታጠበ እጅ ፊታችንን መደባበስና መንካት የለብንም።


የኮሮና ቫይረስ በሚከተሉት ነገሮች ከፊት ለፊታቸው የተጻፉን የጊዜ ርዝመቶ ሳይሞት በሕይወት መቆየት ይችላል። ስለዚህ የተጠቀሱትን እና ሌሎችንም ነገሮች ከነካን፤ ወይም በተጠቀሱት አካባቢዎች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካለፍን ጥንቃቄ ማድረክ አለብን። ካልሆነ ግን ልንጠቃ እንችላለን ማለት ነው።

·          በአየር ላይ፡ = ለ3 (ሦስት) ሰዓታት (አንድ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አፉን ሳይዝ ካስነጠሰ በአካባቢው ላይ ለ3 ሰዓታት ስለሚቆይ በዚያ ካለፍን ልንጠቃ እንችላለን (ስካርብ ወይ ሻፕ መልበስ አፍን እና አፍንጫን መሸፈን መልካም ነው)
·        በመዳብ እና መዳብ ነክ ነገሮች፡ = ለ4 (አራት) ሰዓታት
·        በካርቶን እና ካርቶን ነክ ነገሮች፡ = ለ24 (ለሃያ ዐራት) ሰዓታት
·        በብረትና ብረት ነክ ነገሮች፡ = ከ2-3 (ከሁለት እስከ ሦስት) ቀናት
·        በፕላስቲክ እና ፕላስቲክ ነክ ነገሮች፡= ከ2-3 (ከሁለት እስከ ሦስት) ቀናት ሳይሞት መቆየት ይችላል።
ይህ የሚያሳየን የምንነካው ሁሉ ስጋት ያለው ስለሆነ፡   እጃችንን ሳንታጠብ ምግብ አንደማንበላ ሁሉ በተጠቀሰው ዓይነት መንገድ እጆቻችንን ሳንታጠብ ፊታችችንን መንካት የለብንም።

video: 
ልዑል አምላክ በቸርነቱ  ይጠብቀን

ከአውደ ጥናት

Friday, March 13, 2020

ራሰዎን ይጠብቁ!


ኮሮና ባይረስ የተባለውን አና በዓለም ኣቀፍ ደረጃ አየተዛመተ ያለውን ወረርሽ ለመከላከል የጤና ባለሙያዎች የሚከተሉትን ማድረግ አንዳለብን ይናገራሉ፥

1.      አጆቻችንን በሳሙና አና በውሀ አዘውትረን በተለይ ማነኛውንም ነገር በአጃችን ከነካን በኍላ ቢያንስ ለ20(ሃያ) ሰከንድ ያህል መታጠብ፡ ውሀ ካላገኘን የ’አጅ ማጽጃ ኣልኮል መጠቀም ሳንታጠብ ፊታችን በተለይ (ዓናችንን፡ኣፍንጫችንን አና አፋችንን መንካት የለብንም)
2.     ባልታጠበ አጅ ዐይናችሁን፣ አፍንጫችሁን፡ አና አፋችሁን ከመነካካት ተቆጠቡ
3.     ከታመሙ ፡ ተጠርጣሪዎች ወይም በቫይረሱ ለመያዝ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች ጋር (ከማናውቃቸው) የቅርብ ንክኪ ከማድረግ ከመቀራረብ ተቆጠቡ
4.     ከታመሙ ማለትም የህመም ስሜት ከተሰማዎ ከቤተዎ ኣይውጡና ወደ ሐኪመዎ ይደውሉ
5.     በሚያስሉና በሚያስነጥሱ ጊዜ አፈዎን በሶፍት ወረቀት ይሸፍኑ ከዚያ በኍላ ሶፍቱን ወደ ቆሻሻ መጣያ ይጣሉትና እጆቼዎን ይታጠቡ
6.     የሚነካኩ ቦታዎችን፣ መቀመጫዎችን፡ ጠረጴዛዎችን፣መዝጊያ። ቁልፍ፣ ቦርሳ፣ ስክብሪቶ፣ስልክ፣ ወዘተ አዘውትራችሁ በማጽዳት ቫይረስና ጀርሞችን አስወግዱ
7.     የጉንፋን ክትባት(ፍሉ ቫክሲን) ያልወሰዳችሁ ውሰዱ፤

·        6 ኢንች ወይም 183 cent meter (መቶ ሰማንያ ሦስት ሴንቲ ሜትር ) ርቀት ከሰዎች ርቀን መቆም፡ መቀመጥ ወይም መራመድ ይኖርብናል ፤(ምክንያቱም በማስነጠስና በመሳል ጊዜ፡ መመነካካትም ሕመሙን ልንወስድ አንችላለን)

መረጃ/COVID-19

የጤና ባለሙያዎች አና የጤና ድርጅቶች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች አንድናደርግ ይመክራሉ


The CDC is closely monitoring an outbreak of respiratory illness caused by this new coronavirus. The outbreak first started in Wuhan, China, but cases have been identified in a growing number of other international locations, including the United States. The Red Cross will closely monitor guidance from the CDC to determine the need for additional safety steps or updates to these guidelines. Up-to-date information from the CDC can be found at cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/.The below guidelines provide guidance to managers, employees and volunteers in handling and addressing issues and questions related to the 2019 coronavirus.

General Health and Safety The best way to prevent infection is to avoid being exposed to this coronavirus. However, as a reminder,
 CDC always recommends everyday preventive actions to help prevent the spread of respiratory viruses, including:
Wash your hands often with soap and water for at least 20 seconds. Use an alcohol-based hand sanitizer that contains at least 60% alcohol if soap and water are not available
.Avoid touching your eyes, nose, and mouth with unwashed hands
.Avoid close contact with people who are sick
.Stay home when you are sick
.Cover your cough or sneeze with a tissue, then throw the tissue in the trash
.Clean and disinfect frequently touched objects and surfaces. In addition to preventing the spread of germs, as it is currently flu and respiratory disease season,
The CDC recommends getting vaccinated and taking flu antivirals if prescribed.
While there is no vaccine for coronavirus at this time, preventing the spread of any respiratory infection will help employees, volunteers and colleagues stay healthier during this period of seasonal illness

ኮሮና ባይረስ የተባለውን አና በዓለም ኣቀፍ ደረጃ አየተዛመተ ያለውን ወረርሽ ለመከላከል የጤና ባለሙያዎች የሚከተሉትን ማድረግ አንዳለብን ይናገራሉ፥
1.      አጆቻችንን በሳሙና አና በውሀ አዘውትረን በተለይ ማነኛውንም ነገር በአጃችን ከነካን በኍላ ቢያንስ ለ20(ሃያ) ሰከንድ ያህል መታጠብ፡ ውሀ ካላገኘን የ’አጅ ማጽጃ ኣልኮል መጠቀም ሳንታጠብ ፊታችን በተለይ (ዓናችንን፡ኣፍንጫችንን አና አፋችንን መንካት የለብንም)
2.     ባልታጠበ አጅ ዐይናችሁን፣ አፍንጫችሁን፡ አና አፋችሁን ከመነካካት ተቆጠቡ
3.     ከታመሙ ፡ ተጠርጣሪዎች ወይም በቫይረሱ ለመያዝ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች ጋር (ከማናውቃቸው) የቅርብ ንክኪ ከማድረግ ከመቀራረብ ተቆጠቡ
4.     ከታመሙ ማለትም የህመም ስሜት ከተሰማዎ ከቤተዎ ኣይውጡና ወደ ሐኪመዎ ይደውሉ
5.     በሚያስሉና በሚያስነጥሱ ጊዜ አፈዎን በሶፍት ወረቀት ይሸፍኑ ከዚያ በኍላ ሶፍቱን ወደ ቆሻሻ መጣያ ይጣሉት
6.     የሚነካኩ ቦታዎችን፣ መቀመጫዎችን፡ ጠረጴዛዎችን ወዘተ አዘውትራችሁ በማጽዳት ቫይረስና ጀርሞችን አስወግዱ
7.     የጉንፋን ክትባት(ፍሉ ቫክሲን) ያልወሰዳችሁ ውሰዱ፤

·        6 ኢንች ወይም 183 cent meter (መቶ ሰማንያ ሦስት ሴንቲ ሜትር ) ርቀት ከሰዎች ርቀን መቆም፡ መቀመጥ ወይም መራመድ ይኖርብናል ፤(ምክንያቱም በማስነጠስና በመሳል ጊዜ፡ መመነካካትም ሕመሙን ልንወስድ አንችላለን)

Saturday, February 29, 2020

የአውደ ጥናት ልዩ ወዳጅ መሆን ይፈልጋሉ/Do you want to be Special Member of Awde Tinat?

የአውደ ጥናት ልዩ አባል በመሆን አውደ ጥናትን ይርዱ



ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

ዛሬ የምነግራችሁ ለየት ያለ አዲስና መልካም ዜና ወይም ማስታዎቂያ አለኝ። ከዩቱብ ለዚህ ቻናል የተሰጠ መልካም ዕድል ነው። ዕድሉ እናንተንም እኔንም ያስደስታል ብየ አምናለሁ።

ይኸውም በዩቱብ በኩል መመዘኛውን ላሟሉ የዩቱብ ተጠቃሚዎች የሚሰጥ ልዩ ዕድል ንው። “ቻናል መምበር ሺፕ” ይባላል፤ የቻናል አባልነት ማለት ነው። አንድ የዩቱብ ቻናል ብዙ ሰዎች የሚፈልጉትና የሚመለከቱት ሆኑ ሲገኝ ይህ ዕድል ይሰጠዋል። ማለትም አገልግሎቱን የሚወዱና የሚደግፉ ሰዎች አገልግሎቱን በመደገፍ መሳተፍ የሚችሉበት ልዩ መንገድ ነው፡።

ይህ ፕሮግራም የተፈጠረበት ዋና አላማ አንድ የዩቱብ ተጠቃሚ  ወይም በዩቱብ የሚተላለፍ ዝግጅት ብዙ ተመልካቾች ያሉት ሲሆንና የዝግጅቱ ተፈላጊነት በዩቱም ሐላፊዎች ሲታመንበት ዝግጅቱ በተሟላ መልኩ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ተመልካቾች በበጎ ፈቃድ ብቻ መርዳት እንዲችሉ አመች መንገድን ለመፍጠር ሲባል ነው።

ስለዚህ በዚህ ፕሮግራም የሚተላለፈውን ዝግጅት ወይም ትምህርት የሚከታተሉ እና የሚተላለፈው ዝግጅት ለትውልድ ጠቃሚ በመሆኑ በተሻለ መልኩ መቀጠላለበት ብለው የሚያምኑ ሰዎች በፈቃደኝነት በየወሩ በጣም ትንሽ የሆነ ክፍያን በመክፈል መርዳት ይችላሉ። የአባልነት ደረጃዎችና የክፍያ መጠኑም ሦስት ዓይነት ሲሆን የሚከተለውን ይመስላል።

የአባልነት ደረጃው ደረጃ አንድ፤ ደረጃ ሁለት፤ እና ደረጃ ሦስት በመባል በ ሦስት ይከፈላል፡
ደረጃ አንድ አባልነት $3.99
ደረጃ ሁለት አባልነት $5.99 እና
ደረጃ ሦስት አባልነት $9.99 በየወሩ ይከፈላል

 ይህ ክፍያ ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተና እንደ ድጋፍ ወይም ጉርሻ የሚቆጠር እንጂ የአገልግሎት ወይም ለሚተላለፈው ዝግጅት ዋጋ በመሆን የሚከፈል አይደለም። ምክንያቱም ሳይከፍሉ መከታተል የሚችሉት ዝግጅት ነው የሚተላለፈው። የሚከፍሉም ሆኑ የማይከፍሉ ሰዎችም የሚከታተሉት አንድ ዓይነት ዝግጅትን ነው እንጅ የተለየ ሁለት ወይም ሦስት ዓይነት ደረጃ ያለው ትምህርት አይተላለፍም።

ይህ እንዳለ ሆኖ ግን አባላቱ ለበጎ አድራጎታቸውና ለታማኝነታቸው እንደ ልዩ ወዳጅ ስለሚቆጠሩ እንደ ማነኛውም የአውደ ጥናት ተከታታዮች ሳይሆን እንደ ልዩ ቤተሰብ ስለሚቆጠሩ  ከሌሎቹ ለየት ያሉ ነገሮችን ያገኛሉ። በዩቱብ ሕግ መሠረትም እነዚህ ልዩ አባላት የሚያገኟቸው ጥቃቅን ጥቅማ ጥቅሞች በግልጽ እንደ መብት ሆነው የተጻፉላቸው ናቸው። እነዚህም
1.  በወር አንድ ጊዜ ለልዩ አባላት ብቻ በልዩ ልዩ አርእስት ዙሪያ የቀጥታ ሥርጭት ይቀርብላቸዋል::

2.  በአውደ ጥናት ውስጥ አስተያየት ሲሰጡና ልዩ ልዩ ተሳትፎ ሲያደርጉ ለነሱ ብቻ የተዘጋጀ ልዩ መታወቂያና በሥዕላዊ መግለጫ የተዘጋጀ አርማ ይሰጣቸዋል። ስለዚህ በአውደ ጥናት  አንድ ነገር በሚጽፉ ጊዜ ደምቀው ይታያሉ፤ ተሳትፏቸው ሁሉ ከሌሎች ጎልቶ ወይም ልቆ ይታያል።

በመሆኑም አውደ ጥናትን የምትወዱ በተለይ የግእዝን ቋንቋ የምትከታተሉና ይህ አምላካዊና የጥበብ ቋንቋ የሆነ “የጋራ ቋንቋችን” ልሣነ ግእዝ ለትውልድ እንዲተላለፍ የምትፈልጉ ሁሉ ይህንን መልካም አጋጣሚ ተጠቅማችሁ የአውደ ጥናት ልዩ ወዳጅና አባል በመሆን አውደ ጥናትን ለመርዳት እንድትመዘገቡ  አውደ ጥናት ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

እንኳን ወደ አውደ ጥናት ዘግእዝ በሰላም መጣችሁ ከሁሉ በላ የአውደ ጥናት ልዩ ወዳጆች በመሆን በልዩ አባልነት ስለተመዘገባችህ አመሰግናለሁ እንዲሁም ይህንን በጎ ተግባር ለመሥራት እግዚአብሔር ስላስቻላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።

የአውደ ጥናት ልዩ አባላት በመሆናችሁም የምታቀርቡት አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ጎልቶ የሚታይ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ላረጃግጥላችሁ እወዳለሁ። ለአውደ ጥናት የምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ ለአውደ ጥናት እድገትና መስፋፋት በተለይ የጋራ ቋንቋችን የሆነው የግእዝ ቋንቋ እንደገና እንዲያብብ ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

በአውደ ጥናት ወይም በእኔ በኩልም በወር አንድ ጊዜ ለናንተ ብቻ የሚዘጃጅ በአብዛኛዎቻችሁ ምርጫ የሚቀር ልዩ የቀጥታ ስርጭት ይደረጋል። በሚደረገው ሥርጭትም ከልዩ አባላት መካከል በቀጥታ ሥርጭቱ በተመልካችነት ብቻ ሳይሆን በአዘጋጅነትም መሳተፍ የሚፈልግ መሳተፍ ይችላል።

 ባለፈው እንደ ገለጽኩትም ለናንተ ብቻ የተዘጋጁ በአውደ ጥናት ኮሜንት ወይም አስተያየት ስትጽፉ ጽሁፋችሁ ጎልቶና ደምቆ የሚታይ ይሆናል። ልዑል አምላክ አእምሮውን ለብዎውን ያድለን በሰላም ያቆየን፤ በድጋሚ እንኳን የአውደ ጥናት ልዩ አባላት ለመሆን ቻልን ። አመሰግናለሁ። ቪዲዮውን ለመስማትና ሰብስክራይብ ለማድረግ የሚከተለውን ይጫኑ

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት

Friday, February 28, 2020

የትምህርት ማስታዎቂያ የግእዝ ትምህርት 2ኛ ዙር ምዝገባ/Registration for Ge'ez language 2nd round class


የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ምዝገባ ማስታዎቂያ





ሰላም ለኵልክሙ ፍቁራነ አውደ ጥናት!


አውደ ጥናት ዘግእዝ ሁለተኛውን ዙር የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ለ1ኛ እና ለ2ኛ ደረጃ የግእዝ ቋንቋ ተማሪዎች ግንቦት አንድ ቀን ለመጀመር ምዝገባ ተጀምሯል። ስለዚህ 1ኛ ዙር ያመለጣችሁ ተማሪዎች አሁኑኑ መመዝገብ ትችላላችሁ።   ለበለጠ ማብራርያ ወይም ለመመዝገብ  መሚከተሉት ያገኙናል።


1.  +1 703 254 6601 ይደውሉ ( ከአሜሪካና ካናዳ ውጭ የምትኖሩ በዋትስአፕ፣ በኢሞ፣ ወይም በባይቨር በነጻ መደወል ይቻላል)
2.  Learngeez@outlook.com ኢሜይል መላክ ትችላላችሁ
3.  በዚህ “አዋጅ” በተሰኘው “አውደ መጣጥፍ” በአስተያየት መስጫ ቦታ መልዕክት ያስቀምጡ

Wednesday, February 26, 2020

የሚከራይ ቤት ወይም ክፍል/House or Room for Rent

የሚከራይ ቤት/ምድር ቤት/Basement for rent

የሚከራይ ቤት ውድብርጅ ቪርጂኒያ

የሚከራይ ኣንድ ክፍል/Basment/ምድር ቤት የሚከተሉት ሁሉ ያሉት 

  • አዲስ ምኝታ ቤት ከታጣፊ ኣልጋ ጭምር
  • ባለመዝጊያ የልብስ መስቀያ/ክሎሴት
  • ሳሎን፣ሶፋና ጤረጴዛ
  •  መታጠቢያና መጸዳጃ ቤት
  • የራሱ መውጫ በር ያለው
  • ፍርጅ እና ሶፋ ያለው
  • ማጠቢያና ማድረቂያ ማሽን
  •  ኢንተርኔት 24 ሰዓት ያለው
  • የአንድ መኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው
  • ማድቤት የጋራ (ከፈለጉም በኤሌትሪክ ማብሰል ይችላሉ)
ክ2ኛ ፎቅ ላይም ኣንድ የተሟላ ክፍል ኣለን ይጠይቁ
ለመነጋገር በ 703 254 6601 ደውለው ይጠይቁ Address: Woodbridge, VA 22192

አዋጅ ምንድነው? /What is Awaje?

አዋጅ


አዋጅ” የተሰኘው ይህ ድረ-ገጽ በማኅበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች፣ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተክርስቲያናትና ምእመናን ማወቅና ማሳወቅ የሚፈልጓቸውን ማኅበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ሁሉ ያስተዋውቁበትና ያውቁበት ዘንድ  ዘንድ በአውደ ጥናት የተዘጋጀ  ድረ - ገጽ ነው።

የሚከተሉትን በዚህ ድረ-ገጽ በነፃ ማስተዋወቅ ይችላሉ

1. ሃይማኖታዊ ክብረ በአላት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ እና ወርኀዊ በአላትንና ለአብያተ ክርስቲያናት የሚደረጉ ልዩ ልዩ      ዝግጅቶችን ለምሳሌ

·        ሳምንታዊ አገልግሎቶች መርኃ ግብርን
·        የገንዘብ መዋጮ (ፈንድሬይዚንግ)
·        የወንጌል ትምህርት
·        የበአላት ዝግጅት ስብሰባ
·        አጿማትና በአላት የሚውሉባቸውን ቀናት ወዘ ተርፈ


2.  ማኅበራዊ ጉዳዮች

ለሕዝብ ጥቅምና አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ለምሳሌ

·        የሚከራዩ ቤቶች
·        ክፍት የሥራ ቦታዎች
·        ለብዙኃኑ ጥቅምን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ስብሰባዎች
·        ለአዋቂዎችም ሆነ ለሕጻናት የትምህርት አገልግሎትን የሚሰጡ ተቋማት


ሌሎችም ያልተጠቀሱ ለብዙኃኑ ጥቅም ይውላሉ ተብሎ የሚታመንባቸው ሥራዎች ሁሉ በዚህ “አዋጅ” በተሰኘው ድረገጽ ሊተዋወቁ ይችላሉ፤ በ “አዋጅ” ማስተዋወቅ ሲፈልጉ በሚከተለው ስልክ ደውለው “አውደ ጥናትን” ያነጋግሩ። 703 254 6601(call or text) ሠናይ ለክሙ ወስብሐት ለእግዚአብሔር  ከአውደ ጥናት።


ከአውደ ጥናት ዘግ አዝ የግ አዝን ቋንቋ ይማሩ/

Learn Geez language from "Awde Tinat ZeGeez"