Saturday, February 29, 2020

የአውደ ጥናት ልዩ ወዳጅ መሆን ይፈልጋሉ/Do you want to be Special Member of Awde Tinat?

የአውደ ጥናት ልዩ አባል በመሆን አውደ ጥናትን ይርዱ



ሰላም ጤና ይስጥልኝ ከአውደ ጥናት ዘግእዝ ነው

ዛሬ የምነግራችሁ ለየት ያለ አዲስና መልካም ዜና ወይም ማስታዎቂያ አለኝ። ከዩቱብ ለዚህ ቻናል የተሰጠ መልካም ዕድል ነው። ዕድሉ እናንተንም እኔንም ያስደስታል ብየ አምናለሁ።

ይኸውም በዩቱብ በኩል መመዘኛውን ላሟሉ የዩቱብ ተጠቃሚዎች የሚሰጥ ልዩ ዕድል ንው። “ቻናል መምበር ሺፕ” ይባላል፤ የቻናል አባልነት ማለት ነው። አንድ የዩቱብ ቻናል ብዙ ሰዎች የሚፈልጉትና የሚመለከቱት ሆኑ ሲገኝ ይህ ዕድል ይሰጠዋል። ማለትም አገልግሎቱን የሚወዱና የሚደግፉ ሰዎች አገልግሎቱን በመደገፍ መሳተፍ የሚችሉበት ልዩ መንገድ ነው፡።

ይህ ፕሮግራም የተፈጠረበት ዋና አላማ አንድ የዩቱብ ተጠቃሚ  ወይም በዩቱብ የሚተላለፍ ዝግጅት ብዙ ተመልካቾች ያሉት ሲሆንና የዝግጅቱ ተፈላጊነት በዩቱም ሐላፊዎች ሲታመንበት ዝግጅቱ በተሟላ መልኩ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ተመልካቾች በበጎ ፈቃድ ብቻ መርዳት እንዲችሉ አመች መንገድን ለመፍጠር ሲባል ነው።

ስለዚህ በዚህ ፕሮግራም የሚተላለፈውን ዝግጅት ወይም ትምህርት የሚከታተሉ እና የሚተላለፈው ዝግጅት ለትውልድ ጠቃሚ በመሆኑ በተሻለ መልኩ መቀጠላለበት ብለው የሚያምኑ ሰዎች በፈቃደኝነት በየወሩ በጣም ትንሽ የሆነ ክፍያን በመክፈል መርዳት ይችላሉ። የአባልነት ደረጃዎችና የክፍያ መጠኑም ሦስት ዓይነት ሲሆን የሚከተለውን ይመስላል።

የአባልነት ደረጃው ደረጃ አንድ፤ ደረጃ ሁለት፤ እና ደረጃ ሦስት በመባል በ ሦስት ይከፈላል፡
ደረጃ አንድ አባልነት $3.99
ደረጃ ሁለት አባልነት $5.99 እና
ደረጃ ሦስት አባልነት $9.99 በየወሩ ይከፈላል

 ይህ ክፍያ ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተና እንደ ድጋፍ ወይም ጉርሻ የሚቆጠር እንጂ የአገልግሎት ወይም ለሚተላለፈው ዝግጅት ዋጋ በመሆን የሚከፈል አይደለም። ምክንያቱም ሳይከፍሉ መከታተል የሚችሉት ዝግጅት ነው የሚተላለፈው። የሚከፍሉም ሆኑ የማይከፍሉ ሰዎችም የሚከታተሉት አንድ ዓይነት ዝግጅትን ነው እንጅ የተለየ ሁለት ወይም ሦስት ዓይነት ደረጃ ያለው ትምህርት አይተላለፍም።

ይህ እንዳለ ሆኖ ግን አባላቱ ለበጎ አድራጎታቸውና ለታማኝነታቸው እንደ ልዩ ወዳጅ ስለሚቆጠሩ እንደ ማነኛውም የአውደ ጥናት ተከታታዮች ሳይሆን እንደ ልዩ ቤተሰብ ስለሚቆጠሩ  ከሌሎቹ ለየት ያሉ ነገሮችን ያገኛሉ። በዩቱብ ሕግ መሠረትም እነዚህ ልዩ አባላት የሚያገኟቸው ጥቃቅን ጥቅማ ጥቅሞች በግልጽ እንደ መብት ሆነው የተጻፉላቸው ናቸው። እነዚህም
1.  በወር አንድ ጊዜ ለልዩ አባላት ብቻ በልዩ ልዩ አርእስት ዙሪያ የቀጥታ ሥርጭት ይቀርብላቸዋል::

2.  በአውደ ጥናት ውስጥ አስተያየት ሲሰጡና ልዩ ልዩ ተሳትፎ ሲያደርጉ ለነሱ ብቻ የተዘጋጀ ልዩ መታወቂያና በሥዕላዊ መግለጫ የተዘጋጀ አርማ ይሰጣቸዋል። ስለዚህ በአውደ ጥናት  አንድ ነገር በሚጽፉ ጊዜ ደምቀው ይታያሉ፤ ተሳትፏቸው ሁሉ ከሌሎች ጎልቶ ወይም ልቆ ይታያል።

በመሆኑም አውደ ጥናትን የምትወዱ በተለይ የግእዝን ቋንቋ የምትከታተሉና ይህ አምላካዊና የጥበብ ቋንቋ የሆነ “የጋራ ቋንቋችን” ልሣነ ግእዝ ለትውልድ እንዲተላለፍ የምትፈልጉ ሁሉ ይህንን መልካም አጋጣሚ ተጠቅማችሁ የአውደ ጥናት ልዩ ወዳጅና አባል በመሆን አውደ ጥናትን ለመርዳት እንድትመዘገቡ  አውደ ጥናት ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

እንኳን ወደ አውደ ጥናት ዘግእዝ በሰላም መጣችሁ ከሁሉ በላ የአውደ ጥናት ልዩ ወዳጆች በመሆን በልዩ አባልነት ስለተመዘገባችህ አመሰግናለሁ እንዲሁም ይህንን በጎ ተግባር ለመሥራት እግዚአብሔር ስላስቻላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።

የአውደ ጥናት ልዩ አባላት በመሆናችሁም የምታቀርቡት አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ጎልቶ የሚታይ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ላረጃግጥላችሁ እወዳለሁ። ለአውደ ጥናት የምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ ለአውደ ጥናት እድገትና መስፋፋት በተለይ የጋራ ቋንቋችን የሆነው የግእዝ ቋንቋ እንደገና እንዲያብብ ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

በአውደ ጥናት ወይም በእኔ በኩልም በወር አንድ ጊዜ ለናንተ ብቻ የሚዘጃጅ በአብዛኛዎቻችሁ ምርጫ የሚቀር ልዩ የቀጥታ ስርጭት ይደረጋል። በሚደረገው ሥርጭትም ከልዩ አባላት መካከል በቀጥታ ሥርጭቱ በተመልካችነት ብቻ ሳይሆን በአዘጋጅነትም መሳተፍ የሚፈልግ መሳተፍ ይችላል።

 ባለፈው እንደ ገለጽኩትም ለናንተ ብቻ የተዘጋጁ በአውደ ጥናት ኮሜንት ወይም አስተያየት ስትጽፉ ጽሁፋችሁ ጎልቶና ደምቆ የሚታይ ይሆናል። ልዑል አምላክ አእምሮውን ለብዎውን ያድለን በሰላም ያቆየን፤ በድጋሚ እንኳን የአውደ ጥናት ልዩ አባላት ለመሆን ቻልን ። አመሰግናለሁ። ቪዲዮውን ለመስማትና ሰብስክራይብ ለማድረግ የሚከተለውን ይጫኑ

ልዑል አምላክ ማስተዋሉን ያድለን
ከአውደ ጥናት

Friday, February 28, 2020

የትምህርት ማስታዎቂያ የግእዝ ትምህርት 2ኛ ዙር ምዝገባ/Registration for Ge'ez language 2nd round class


የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ምዝገባ ማስታዎቂያ





ሰላም ለኵልክሙ ፍቁራነ አውደ ጥናት!


አውደ ጥናት ዘግእዝ ሁለተኛውን ዙር የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ለ1ኛ እና ለ2ኛ ደረጃ የግእዝ ቋንቋ ተማሪዎች ግንቦት አንድ ቀን ለመጀመር ምዝገባ ተጀምሯል። ስለዚህ 1ኛ ዙር ያመለጣችሁ ተማሪዎች አሁኑኑ መመዝገብ ትችላላችሁ።   ለበለጠ ማብራርያ ወይም ለመመዝገብ  መሚከተሉት ያገኙናል።


1.  +1 703 254 6601 ይደውሉ ( ከአሜሪካና ካናዳ ውጭ የምትኖሩ በዋትስአፕ፣ በኢሞ፣ ወይም በባይቨር በነጻ መደወል ይቻላል)
2.  Learngeez@outlook.com ኢሜይል መላክ ትችላላችሁ
3.  በዚህ “አዋጅ” በተሰኘው “አውደ መጣጥፍ” በአስተያየት መስጫ ቦታ መልዕክት ያስቀምጡ

Wednesday, February 26, 2020

የሚከራይ ቤት ወይም ክፍል/House or Room for Rent

የሚከራይ ቤት/ምድር ቤት/Basement for rent

የሚከራይ ቤት ውድብርጅ ቪርጂኒያ

የሚከራይ ኣንድ ክፍል/Basment/ምድር ቤት የሚከተሉት ሁሉ ያሉት 

  • አዲስ ምኝታ ቤት ከታጣፊ ኣልጋ ጭምር
  • ባለመዝጊያ የልብስ መስቀያ/ክሎሴት
  • ሳሎን፣ሶፋና ጤረጴዛ
  •  መታጠቢያና መጸዳጃ ቤት
  • የራሱ መውጫ በር ያለው
  • ፍርጅ እና ሶፋ ያለው
  • ማጠቢያና ማድረቂያ ማሽን
  •  ኢንተርኔት 24 ሰዓት ያለው
  • የአንድ መኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው
  • ማድቤት የጋራ (ከፈለጉም በኤሌትሪክ ማብሰል ይችላሉ)
ክ2ኛ ፎቅ ላይም ኣንድ የተሟላ ክፍል ኣለን ይጠይቁ
ለመነጋገር በ 703 254 6601 ደውለው ይጠይቁ Address: Woodbridge, VA 22192

አዋጅ ምንድነው? /What is Awaje?

አዋጅ


አዋጅ” የተሰኘው ይህ ድረ-ገጽ በማኅበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች፣ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተክርስቲያናትና ምእመናን ማወቅና ማሳወቅ የሚፈልጓቸውን ማኅበራዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ሁሉ ያስተዋውቁበትና ያውቁበት ዘንድ  ዘንድ በአውደ ጥናት የተዘጋጀ  ድረ - ገጽ ነው።

የሚከተሉትን በዚህ ድረ-ገጽ በነፃ ማስተዋወቅ ይችላሉ

1. ሃይማኖታዊ ክብረ በአላት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ እና ወርኀዊ በአላትንና ለአብያተ ክርስቲያናት የሚደረጉ ልዩ ልዩ      ዝግጅቶችን ለምሳሌ

·        ሳምንታዊ አገልግሎቶች መርኃ ግብርን
·        የገንዘብ መዋጮ (ፈንድሬይዚንግ)
·        የወንጌል ትምህርት
·        የበአላት ዝግጅት ስብሰባ
·        አጿማትና በአላት የሚውሉባቸውን ቀናት ወዘ ተርፈ


2.  ማኅበራዊ ጉዳዮች

ለሕዝብ ጥቅምና አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ለምሳሌ

·        የሚከራዩ ቤቶች
·        ክፍት የሥራ ቦታዎች
·        ለብዙኃኑ ጥቅምን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ስብሰባዎች
·        ለአዋቂዎችም ሆነ ለሕጻናት የትምህርት አገልግሎትን የሚሰጡ ተቋማት


ሌሎችም ያልተጠቀሱ ለብዙኃኑ ጥቅም ይውላሉ ተብሎ የሚታመንባቸው ሥራዎች ሁሉ በዚህ “አዋጅ” በተሰኘው ድረገጽ ሊተዋወቁ ይችላሉ፤ በ “አዋጅ” ማስተዋወቅ ሲፈልጉ በሚከተለው ስልክ ደውለው “አውደ ጥናትን” ያነጋግሩ። 703 254 6601(call or text) ሠናይ ለክሙ ወስብሐት ለእግዚአብሔር  ከአውደ ጥናት።


ከአውደ ጥናት ዘግ አዝ የግ አዝን ቋንቋ ይማሩ/

Learn Geez language from "Awde Tinat ZeGeez"